Fana: At a Speed of Life!

በባህል ቱሪዝም እና ስፖርት የመማክርት ጉባዔ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህል ቱሪዝም እና ስፖርት የመማክርት ጉባዔ መመስረቱን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
መመክርቱ ባህል ፣ቱሪዝም እና ስፖርት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን ጠቀሜታ ለማሳደግ መመስረቱ ተገልጿል፡፡
በመመስረቻ ጉባኤው የአማካሪ ጉባኤ ማቋቋሚያ መመሪያ፣ አላማ፣ የተፈፃሚነት ወሰን ፣ የአማካሪው ተግባርና ሃላፊነት የአማካሪ አባላት መምረጫ መስፈርቶችና አሰያየም ፣ የአማካሪ አባላት ብዛት፣ የአማካሪ አባላት አሰራር እና ልዩ ልዩ ድንጋጌወች ቀርበዉ ውይይት ተደርጎባቸዋል ፡፡
የመማክርት ጉባኤው ከየዘርፉ የተውጣጡ 45 አባላት ያሉት ሲሆን ከጉባኤውም ዘጠኝ አባላት ያሉት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማቋቋም ሰብሳቢ ምክትል ሰብሳቢ እና ጸሀፊ በመምረጥ መጠናቀቁን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.