የሀገር ውስጥ ዜና

ህብረተሰቡ ሃሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን አውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

By Tibebu Kebede

May 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጀለኞች ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ፅህፈት ቤቱ ህብረተሰቡ ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስቧል፡፡

ከዚህ ባለፈም እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና ጥፋት የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎችን ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅም ጥሪውን አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!