የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

May 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሪታ ላራንጂንሃ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍና ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብ በሚቻልበቸው መንገዶች ላይ  ትኩረቱን ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዳይሬክተሯ  የአውሮፓ ህብረት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍና ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የአጭርና ረጅም ጊዜ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሰራ መናገራቸውን ከሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!