Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያን የአፍሪካ ተምሳሌት አድርገው ካቆዩ የአርበኞች ታሪክ ልምድ በመውሰድ የአሁኑ ትውልድ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ኢትዮጵያን ማሻገር ይኖርበታል “-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 80ኛው የአርበኞች ቀንን በማስመልከት በአርበኞች ስም የተሰየሙ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።
ምክትል ከንቲባዋ የራስ ደስታ ሆስፒታል ፣አርበኞች እና የሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤቶችን ነው  የጎበኙት፡፡
በጉብኝታቸው ተቋማቱ የተሰየሙበትን አላማ ለትውልዱ ማሳወቅ ያስፈልጋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አባት አርበኞች ወራሪውን በመከከት የኢትዮጵያን አንድነት ጠብቀው አስረክበውናል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የአሁኑ ትውልድም የሀገርን አንድነት ጠብቆ የአባቶቻችንን ታሪክ በልማቱም በመድገም ኢትዮጵያን ለማሻገር የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.