የሀገር ውስጥ ዜና

80ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል ተከበረ

By Meseret Awoke

May 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 80ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል ተከበረ።

ጣሊያን የአድዋን ድል ለመበቀል በሚል በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አማካኝነት፥ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን መውረሯ የሚታወስ ነው።

በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም ወራሪውን ሀይል ለአምስት ዓመታት በጽናት ታግለው 1933 ዓ.ም ድል ነስተውታል።

የወቅቱ አርበኞች ለሀገራቸው ነጻነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያስገኙትን ድል ለማሰብም በየአመቱ ሚያዚያ 27 ተከብሮ ይውላል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!