የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

May 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚደንቷ በመልዕክታቸው፤ የጥንት ኢትዮጵያ አርበኞች አገራችን ነጻነትዋን ጠብቃ እንድትኖር አድርገዋል ያሉ ሲሆን፤ ዛሬም አገርን ለመጠበቅና ለመገንባት አርበኝነት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ያለፈውን ጀግንነት የምናቆየው ለዚህ ከተነሳን ነው ሲሉም በትዊተር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!