ዓለምአቀፋዊ ዜና

ማሊያዊቷ እናት በአንድ ጊዜ 9 ልጆችን ተገላገለች

By Meseret Awoke

May 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የማሊ ዜግነት ያላት እናት በአንድ ጊዜ ዘጠኝ ልጆችን መገላገሏ ተሰምቷል፡፡

ሃሊማ ሲሼ የ25 ዓመት ወጣት ማሊያዊ ስትሆን፤ በሞሮኮ ሃገር ሆስፒታል ዘጠኝ ልጆችን መገላገሏን የማሊ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ወጣቷ 7 ልጆችን እንደምትወልድ በአልትራሳውንድ መመርመሪያ ታይቶ ስትጠበቅ የነበረ ቢሆንም፤ አምስት ሴቶችና አራት ወንዶችን በሰላም መገላገል እንደቻለች ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ወቅትም እናት እና የተወለዱት ልጆች በሙሉ ጤና ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ሲቤ የገለጹ ሲሆን፤ ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ከሆስፒታል ይወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!