በደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የምርት ዘመን 12 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት መታቀዱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የምርት ዘመን 12 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት መታቀዱ ተገልጿል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የተዘጋጀ የ2013/2014 የምርት ዘመን የክረምት የሰብል ልማት ስራወች እቅድ የንቅናቄ መድረክ በዞኑ ተካሂዷል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው የዞኑን የምርታማነት ደካማነት በተመለከተ መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።
ዞኑ በአማካኝ በአመት ከ1 ሄክታር መሬት ከ 1 ኩንታል በላይ ማሳደግ እንዳልቻለ የተገለጸ ሲሆን፤ አረም፣ የአስተራረስ ወቅቱን አለመጠበቅ፣ የተባይ በብዛት መከሰትና የአንበጣ መንጋ እንዲሁም የግብአት አቅርቦት ችግር ለምርታማነቱ አለመጨመር በምክንያትነት ተነስቷል።
እነዚህን ችግሮች በመቅረፍና ዘመናዊ መካናይዜሽንን በመጠቀም በዘንድሮው የምርት ዘመን 12ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እቅድ ተይዟል ተብሏል።
ይሄም ካለፈው አመት 2ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ ያለው ሲሆን፤ በአማካኝ በሄክታር 23 ኩንታል ከነበረው ወደ 27 ኩንታል ለማሳደግም ይሰራል ተብሏል።
በይክበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!