Fana: At a Speed of Life!

በተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ መኖሪያ ቤት የአፍጥር ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ መኖሪያ ቤት የአፍጥር ስነ ስርዓት ተካሄደ።

የአፍጥር ስነ ስርዓቱ ከ150 እስከ 200 እንግዶች በተገኙበት ነው የአፍጥር ስነ ስርዓቱ የተካሄደው።

ለተቸገሩ የሰጠ ለፈጣሪ አበደረ በሚል መሪ ቃል ቀጣዮቹን የፆም የመጨረሻ ቀናት ፈጣሪን እርቅ ለመለመን የአፍጥር ስነ ስርዓት እንደሚካሄድም ተነግሯል።

በአፍጥር ስነ ስርዓቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሌሎች እምነት ተከታዮች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.