የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

May 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ፡፡

አቶ ደመቀ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በፕሪቶሪያ በነበራቸው ቆይታ በወቅታዊና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መግባባት ላይ መድረሳቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!