የሀገር ውስጥ ዜና

የከንቲባዎችና የግሉ ዘርፍ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Abrham Fekede

May 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የከንቲባዎችና የግሉ ዘርፍ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከንቲባዎችንና የግሉን ዘርፍ በአንድ ያሰባሰበ ሃገር አቀፍ ስብሰባ ነው ተብሎለታል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ስበሰባውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

“የከተሞች ሚና ለንግድ መስፋፋት፤ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ” በሚል ርዕስ ነው ውይይቱ የሚካሄደው ፡፡

ሃገር አቀፍ ስብሰባው ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከንቲባዎች፣ የንግዱ ዘርፍ አካላት፣ ምሁራንና ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው ልዩ ልዩ አካላትም ተሳታፊዎች ናቸው።

በርካታ የጥናት ወረቀቶችም በስብሰባው ላይ ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡