የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኒጀር ፕሬዚዳንት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ገለጻ አደረጉ

By Abrham Fekede

May 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኒጀር አቻቸው ሞሀመድ ባዞም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ገለጻውን ያደረጉት ኒጀር የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል መሆኗን ተከትሎ ነው፡፡

ኒጀር ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከተወከሉ ሦስት የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ነች፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከህዳሴ ግድቡ ባሻገር በትግራይ ክልል፣ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር እና በመጪው ምርጫ ዙሪያ ገለጻ መስጠታቸውን ከፕሬዚዳንቱ የትዊተር ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!