የሀገር ውስጥ ዜና

ተመድ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 65 ሚሊየን ዶላር ለቀቀ

By Tibebu Kebede

May 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 65 ሚሊየን ዶላር እንዲለቀቅ ወሰነ፡፡

ድጋፉ በሃገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ምግብ፣ መጠለያ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችላል መባሉን የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ዛሬ የተለቀቀው ድጋፍ በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ከ16 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ይውላል ነው የተባለው፡፡

ከተለቀቀው ድጋፍ ውስጥ 40 ሚሊየን ዶላሩ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን፥ ቀሪው ደግሞ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ይውላል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!