Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ ቦርድ የእጩ መተካት፣ መቀየር፣ መለወጥ እና ማንኛውንም አይነት ማሻሻያ የማይቀበል መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእጩ መተካት፣ መቀየር፣ መለወጥ እና ማንኛውንም አይነት ማሻሻያ የማይቀበል መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በመቀበል፣ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም የድምጽ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተል ሎተሪን በማከናወን የእጩዎችን ዝርዝር አጠናቆ ለድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት ሲያዘጋጅ መቆየቱን ገልጿል።

በምርጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 39 (3) የፖለቲካ ፓርቲ እጩውን መለወጥ  ወይም መተካት የሚቻልበት ቀን የእጩ ምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ካለቀ በኋላ ከሆነ ከድምጽ መስጫው ቀን ከአንድ ወር በፊት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል ነው ያለው ቦርዱ።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ከሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእጩ መተካት፣ መቀየር፣ መለወጥ እና ማንኛውንም አይነት ማሻሻያ የማይቀበል መሆኑንም ይገልጻል ብሏል።

እስከአሁን የቀረቡ ከእጩዎች ለውጥ ጋር የተገናኙ ጥያቄዎች የሚስተናገዱ ሲሆን ከዚህ በኋላ የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት እየተከናወነ በመሆኑ እና በህግ የተቀመጠውም ግዴታ በማብቃቱ ከእጩዎች ምዝገባ ጋር የተገናኘ ማንኛውንም አይነት አቤቱታ መቀበል ማቆሙን ፓርቲዎች ተረድተው ከዚህ በፊት ያስገቧቸው የለውጥ ጥያቄዎችን ብቻ እንዲከታተሉ እናስታውቃለን ማለቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል  ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.