Fana: At a Speed of Life!

እስካሁን የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር ከ31 ሚሊየን በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር ከ31 ሚሊየን 724 ሺህ 947 መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 54 በመቶ ወንዶች ሲሆኑ 46 በመቶዎቹ ደግሞ ሴቶች ናቸው።

የመራጮች ምዝገባው በትናትናው ዕለት ለአንድ ሳምንት የተራዘመ ሲሆን፤ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው ጣቢያዎች ቁጥር43 ሺህ 17 መሆኑን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተለያዩ ችግሮች ማጋጠማቸውን የገለፀው ቦርዱ ከእነዚህም መካከል  የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ መጀመር፣ የመራጮች ምዝገባ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የተመዝጋቢዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆን፣ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረ በኃላ የምርጫ ጣቢያዎች እና የተመዝጋቢዎች አለመመጣጠን በተለይ በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በጸጥታ ችግር የተነሳ የመራጮች ምዝገባ ማድረግ ባልተቻለባቸው ቦታዎች በልዩ ሁኔታ የሚደረግ መሆኑ የሚጠቀሱ ናቸው።

የመራጮች ምዝገባ ላይ ላጋጠሙ ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄዎች መስጠቱን እና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.