የሀገር ውስጥ ዜና

ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የቻይና ሮኬት በህንድ ውቂያኖስ ላይ አረፈ

By Tibebu Kebede

May 09, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ ማረፉ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት አስታወቀ።

የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ለኢቲቪ እንደገለፁት የቻይና ሎንግ ማርች 5ቢ ሮኬት ተወሰነ ክፍሉ መሬት ላይ ሳይደርስ የተቃጠለ ሲሆን የቀረው ስብርባሪም በህንድ ውያኖስ ማልዲስ ደሴት አቅራቢያውቅያኖስ ውስጥ አርፏል።

5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ ሲሽከረከ መቆየቱ ይታወሳል።

ኢንስትቲዩቱ ከዚህ በፊት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው በመሬት ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅበት ጊዜ 90 ደቂቃ ሲሆን ፍጥነቱም በስዓት 28 ሺህ ኪ.ሜ ይደርሳል ነው ያለው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!