የሀገር ውስጥ ዜና

ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተለያየ የቢዝነስ መስክ የተሰማሩና ተጽዕኖ ፈጣሪ  ግለሰቦች ጎበኙ

By Feven Bishaw

May 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተለያየ የቢዝነስ መስክ የተሰማሩናተጽዕኖ ፈጣሪ  ግለሰቦች ጎብኝተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ  ሴክታሪያት አማካይነት በተዘጋጀው በዚህ ጉብኝት 40 ከተለያየ ኩባንያዎች የተውጣጡ ስራ ፈጣሪዎች እና ባለቤቶች ተገኝተዋል ።

በጉብኝቱም አጠቃላይ የፕሮጀክቶቹ ፋይዳ፣ የግንባታ ሂደት ፣ የሚፈጥሯቸው ሀገራዊ አቅሞች እና ተያይዘው የሚፈጠሩ እድሎች ተገልጸዋል ።

ጎብኚዎቹ በተለያየ የቢዝነስ መስክ የተሰማሩ በመሆናቸው ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጉብኝቱ  ያግዛቸዋል ተብሏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት እድሳት ፣ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ፣ ከመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት የማስዋብ ስራ ፣ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት እንዲሁም የቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያን ጎብኚዎቹ ተመልክተዋል ።

በዓልአዛር ታደለ