የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ  ልዩ ኃይል ፖሊሶችን አስመረቀ

By Meseret Demissu

May 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይል ፖሊሶችን  ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂ ልዩ ሀይል ፖሊሶች በተጨማሪ የልዩ ኃይል ፖሊሶች መኪና አሽከርካሪዎችም  መመረቃቸው ተመላክቷል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች መታደማቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!