የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢድን በማስመልከት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ድጋፍ አደረጉ

By Abrham Fekede

May 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ በዓልን ለማክበር የሚያግዝ ድጋፍ አደረጉ።

ፕሬዚዳንቷ በዚህ ሳምንት የሚከበረውን የኢድ በዓል ለማክበር የሚያግዙ የተለያዩ የምግብ ድጋፎችን አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ያበረከቱት በዛሬው ዕለት በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ ፕሬዝዳንቷ ላበረከቱት ድጋፍ አመስግነዋል።

ፕሬዝዳንቷ የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ያደረጉት ድጋፍ አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ በመከተል ሰብዓዊነታቸውን እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!