ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ዲቻና ጅማ አባጅፋር አቻ ተለያዩ

By Abrham Fekede

May 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ወላይታ ዲቻና ጅማ አባጅፋር አቻ ተለያይተዋል፡፡

በመጀመሪያ አጋማሽ ጅማ አባጅፋር መሪ መሆን የሚያስችለውን ግብ በፕሪንስ ዋኦንጎ አማካኝነት በ39 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ሆኖም ወላይታ ዲቻ በስንታየሁ መንግስቱ አማካኝነት በ54ኛው ደቂቃ ላይ ቡድኑን አቻ የሚያደርግ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታውን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

ወላይታ ዲቻ በ22 ጨዋታዎች 30 ነጥብ የያዘ ሲሆን 21 ጨዋታዎችን ያደረገው ጅማ አባጅፋር በ14 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ዋንጫ ማንሳቱን ያረጋገጠው ፋሲል ከነማ በ21 ጨዋታዎች 52 ነጥቦችን ሰብስቧል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በ35፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ34 ነጥቦች ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!