የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጠ

By Tibebu Kebede

May 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጠ፡፡

እውቅናና ሽልማቱ የተሰጠው በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 152 ተማሪዎች ነው፡፡

በእውቅናና ሽልማት መርሐ ግበሩ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ጽህፈት ቤጽ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!