ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ቃለ መሃላ ፈጸሙ

By Tibebu Kebede

May 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለቀጣዮቹ ስድስት አመታት ሃገራቸውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ዛሬ በይፋ ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡

ሙሴቬኒ ባለፈው ጥር ወር በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው እለትም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ በአለ ሲመታቸው ተከናውኖ ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡

በበዓለ ሲመቱ ወቅት በመዲናዋ ካምፓላ ከፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የፀጥታ አካላት ጠንካራ ቁጥጥር እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ከትናንት በስቲያ ሰኞም በዓለ ሲመቱን ለማወክ አቅደዋል የተባሉ ከ40 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!