የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሂሩት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት አቀረቡ

By Tibebu Kebede

May 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት አቀረቡ።

ተቀማጭነታቸው በቤልጂየም፣ ብራስልስ ሆኖ በሉግዘምበርግ እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን አቅርበዋል።

በወቅቱም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።