የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከአፍሪካ አምባሳደሮች ተጠሪ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

May 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከአፍሪካ አምባሳደሮች ተጠሪ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ አምባሳደር አዳራሂም አብዱላዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትየጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ፣ ስለ ህዳሴ ግድብ እና ኢትዮ-ሱዳን ጉዳይ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር አዳራሂም አብዱላዬ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፥ የኢትዮጵያ መንግስት የውስጥ ችግሩን በራሱ አቅም ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚደግፉ ጠቅሰው፥ ከድንበር ጋር ያለውን ችግር በድርድር መፍታት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!