Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ኦሮሚያ አራት ዞኖች የመራጮች ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነቀምቴ ከተማን ጨምሮ በምዕራብ ኦሮሚያ አራት ዞኖች የመራጮች ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በተጀመረባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ምዝገባ ከተጀመረበት ከሚያዚያ 29 ቀን ጀምሮ በርካታ የሆነ ተመዝጋቢ የምርጫ ካርድ እየወሰደ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን ሃገራዊ ብሄራዊ ምርጫ ለማከናወን በቅድመ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ መርሃ ግብር መሰረት በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች የምዝገባ ስራው እየተከናወነ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአራቱ የወለጋ ዞኖች ግን በሌሎች አከባቢዎች የተሰራው የምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና የመራጮች ምዝገባ ስራ ከፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ በአንፃሩ ለአንድ ወር ከ15 ቀናት ገደማ ዘግይቶ ነበር፡፡

ቦርዱም በአራቱ የወለጋ ዞኖች የመራጮች ምዝገባ ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 13 ቀን ድረስ እንዲካሄድ ባስቀመጠው መርሃግብር መሰረት ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.