የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር አብርሃም በላይ አሸጎዳ የሚገኘውን የትራክተሮች መገጣጠሚያ ጎበኙ

By Meseret Awoke

May 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አሸጎዳ በሚገኘው የትራክተሮች መገጣጠሚያ ጉብኝት አካሄዱ።

በጉብኝቱ ወቅትም፥ የክልሉ የግብርና ስራ ወደ ነበረበት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት በቴክኖሎጂ የታገዘ እርሻ ለማካሄድ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንዳለ ገልፀዋል።

ይህን ለማድረግ የሚያግዝና ለግብርና ስራዎችን እንደ ግብአት በመሆን የሚያገለግል የትራክተሮች ከመጎብኘት በተጨማሪ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተወያዩ ተጠቅሷል።

የትግራይ ክልል አስተዳደር ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው እና የሁሉም አካላት የላቀ ትኩረት ከሚሹ ተግባራት አንዱ ግብርና መሆኑን በውይይቱ ተገልጿል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!