Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) – ዘጠነኛው አመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
“በሳይንሳዊ ምርምር ዘላቂ እድገትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንሱ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በዩኒቨርስቲው የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዝዳንት ዶክተር መስፍን ቢቢሶ፥ በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ማካፈልና የልምድ ልውውጥ ማድረግ የኮንፈረንሱ ዓላማ መሆኑን ገልፀው የቅርብ ጊዜ የጥናትና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለዘላቂ እድገት ለመጠቀም ሀገራዊ ፖሊሲዎችን መተንተን ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ ወደ 170 ምርምሮች፣ 60 የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች፣ 10 የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መከናወናቸውን ገልፀዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደስ በበኩላቸው ሀገራዊ የምርምር ኮንፈረንሱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰባሰቡት ተመራማሪዎች ያገኟውን የምርምር ውጤቶችን ለህዝቡ ማድረስና ለቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም የሚያስችል ነው።
ተመራማሪዎች እርስ በእርስ በመተባበር ምርምሮችን ለመስራት፣ የምርምር ስራዎችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች የሚታተሙበትን እድል ለማስፋት እንዲሁም የምርምር ስራ በጀት በጋራ በማዋጣት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማቀናጀት ምቹ ሁኔታዎች የሚፈጠሩበት አጋጣሚ እንደሆነ ነው የገለፁት።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የምርምር ስራዎች በተሳታፊዎች የተጎብኙ ሲሆን ኮንፈረንሱ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
በመለሰ ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.