የሀገር ውስጥ ዜና

በመቐለ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ጊዜያዊ መጠለያ እየተሰራ ነው- ዶ/ር አብርሃም በላይ

By Tibebu Kebede

May 14, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)- በመቐለ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ጊዜያዊ መጠሊያ እየተሰራ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስታወቁ።

ዘላቂ መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ክረምት ሳይገባ ጊዜያዊ መጠለያው ይገነባል ብለዋል፡፡

መጠልያው በሚገነባበት አከባቢ በአካል በመሄድ ማየታቸው፥ ጊዜያዊ መጠሊያው በአስቸኳይ የሚገነባበትን አማራጮች ለማየት ዕድል እንደሰጣቸውን ገልጸው በፍጥነት ለመገንባት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ  እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ፅፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!