ዩ ኤስ ኤይድ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁሶችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከ800 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁሶችን ለትግራይ ክልል እንዲደርስ ለኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡
ድጋፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 40 የጤና ተቋማትና ለሰባት የወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ደርሷል ተብሏል፡፡
ድጋፍ የተደረጉ ቁሳቁሶችን በማድረስ ለተሳተፉ አካላት ድርጅቱ ምስጋና ማቅረቡን ከድርጅቱ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!