ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት አገኘ

By Tibebu Kebede

May 15, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) – የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አባላት የማበረታቻና ሽልማት ፕሮግራም በሀዋሳ ተካሄዷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ማለፋን ተከትሎ ነው የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በጋራ የእውቅናና የማበረታቻ ፕሮግራሙን ያዘጋጁት።

በፕሮግራሙ ላይ ለብሄራዊ ቡድኑ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ማበረታቻ እንደተደረገለት ኮሚሽኑ ገልጿል።

ለዋና አሠልጣኝ 350ሺ፣ለረዳት አሠልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 250 ሺ ፣ለቋሚ ተሰላፊዎች ለእያንዳንዳቸው 250 ሺ፣ ለ5ተቀያሪ ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው 150 ሺ ፣ለኮችንግ ስታፍ አባላት ለእያንዳንዳቸው 100 ሺ እና ለሌሎችም በየደረጃው ማበረታቻ ተደርጎላቸዋል ።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሰው፣ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም በፕሮግራሙ ታድመዋል።

መንጭ:- የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!