የሀገር ውስጥ ዜና

አስትራዜኒካ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተከትበዋል – ጤና ሚኒስቴር

By Meseret Awoke

May 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አስትራዜኒካ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች መከተባቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው እንደገለጹት በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለውን ክትባት በየደረጃው በሁሉም ክልሎች ተዳራሽ ማድረግ በመቻሉ የተከታቢው ቁጥር ጨምሯል።

በአሁኑ ወቅትም ለ1 ሚሊየን 413 ሺህ ሰዎች የአስትራዜኒካ መከላከያ ክትባትን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል መባሉን የዘገበው ኢፕድ ነው።

ክትባቱን ለመስጠት መጀመሪያ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ስለነበረባቸው የመዘግየት ሁኔታ ነበር ያሉት አቶ ዮሐንስ፣ ክትባት ለሚሰጠው የጤና ባለሙያ ሥልጠና መስጠት፤ ለክትባቱ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችም ጊዜ የሚፈልጉ በመሆናቸው ክትባቱን በሁሉም ክልሎች እኩል ማስጀመር እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ጠረፋማ አካባቢዎችን ጨምሮ ከ1 ሺህ በላይ ወረዳዎች ውስጥ ባሉ 20ሺህ የሚጠጉ ቀበሌዎች 6ሺህ የጤና ተቋማት እንዳሉ ያመለከቱት አቶ ዮሐንስ፤ በክትባቱ ሁሉንም ቦታዎች ለማድረስ ከ15 እስከ 20 ቀን መውሰዱን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!