ስፓርት

አቡበከር ናስር የፕሪምየር ሊጉን የግብ አግቢነት ሪከርድን ሰበረ

By Meseret Awoke

May 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አቡበከር ናስር በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል የማስቆጠር ሪከርድን ሰብሯል፡፡

በዛሬው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ላይ 9ኛ፣ 36ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሮ የውድድር ዘመኑ ጎሎቹን ቁጥር 27 አድርሷል፡፡

በዚህም ከወዲሁ በጌታነህ ከበደ በ2009 ተይዞ የነበረውን በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል የማስቆጠር ሪከርድ ማሻሻሉን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!