የሀገር ውስጥ ዜና

ሶስተኛው ዙር የፖለቲካ ፖርቲዎች የምክክር መድረክ ሊካሄድ ነው

By Tibebu Kebede

May 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሶስተኛው ዙር የፖለቲካ ፖርቲዎች የምክክር በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚያከናወን ማይንድ ኢትዮጵያ አስታወቀ ።

ማይንድ ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች የሆነ ሃገራዊ የምክክር መድረኮችን ማመቻቸት አላማ አድርጎ በስምንት ሃገር በቀል ድርጅቶች ጥምረት የተመሰረተ ነው።

እስካሁን የሃገራዊ ምክክር ጽንስ ሃሳብ ሰነድ ዝግጅት፣ ስትራቴጂክ እቅድ፣ ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የስነምግባር ደንብ እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽን ሰነድ ስራዎችን መስራቱንተጠቅሷል።

ማይንድ ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ በቀጣይ ሁሉንም አካታች የሆነ ሃገራዊ የምክክር መድረኮችን ለማዘጋጀት ዝግጅት በማድረግ ላይ ሲሆን በቅርቡም ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 1 ሺህ ዜጎች የሚሳተፉበት መድረክ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!