ቢዝነስ

ሚኒስቴሩ ባለፉት አስር ወራት 238 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰበሰቡን ገለፀ

By Tibebu Kebede

May 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 238 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ።

ገቢው ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ19 ነጥብ 77 በመቶ ወይም የ39 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡

ገቢው የተሰበሰበው ከሀገር ውስጥ ታክስ ፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከሎተሪ ሽያጭ መሆኑም ተገልጿል።

ከሀገር ውስጥ ታክስ 145 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ 92 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር፣ ከሎተሪ ሽያጭ 193 ነጥብ 27 ሚሊየን በላይ ተሰብስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!