Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ አሻራ ሀገርን ታሳቢ ያደረገ እንጂ ምርጫን ያማከለ አይደለም- ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያን እናልብሳት” የ2013 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ባለፉት ሁለት አመታት ተደምረን የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻውን እንዳሳካነው ሁሉ በዚህ አመትም እጅ ለእጅ ተያይዘን ስራውን እናሳካለን” ብለዋል።

አረንጓዴ አሻራ ሀገርን ታሳቢ ያደረገ እንጂ ምርጫን ያማከለ ባለመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ ተማሪዎች እና ሀገር ወዳድ ዜጎች ሁሉ በዚህ ዘመቻ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣው የመሬት መራቆት ሳቢያ ብቻ እስከ 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት በየአመቱ ታጣለች።
ላለፉት ሁለት ዓመታት የተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ስራ ይህን ችግር ከመሠረቱ የሚቀርፍ እንደሆነም በዚህ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በዚህ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ የሚተከል ሲሆን ለጎረቤት ሀገራት ደግሞ 1 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
በአላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.