Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜን አራዝሟል፡፡

ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ ወስኗል።

በዚህ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ https://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ አድራሻን በመጠቀም መመዝገብ እንደሚቻል ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት www.nebe.org.et የምዝገባ አድራሻ ድረ-ገጽ መመዝገብ እንደሚችሉም ነው ያስታወቀው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይህንን የቀጥታ (ኦንላይን) ምዝገባ በማስታወስ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ እንዲያደርጉ ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.