አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር አንድ በሚያደርጉ ዕሴቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል – የሰላም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ግንባት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በልዩነት ላይ ሳይሆን፤ አንድ በሚያደርጉን ዕሴቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡
“የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት፣ ብሔራዊ መግባባት፣ ምርጫ 2013 እና ከዚያ ባሻገር” በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፤ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በልዩነት ላይ ሳይሆን፤ አንድ በሚያደርጉን ዕሴቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሥራት ላይ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለዚህም ሕዝቡ የተጀመረው አገራዊ መግባባት እንዲሳካ በልዩነቶች ላይ ሳይሆን፤ አንድ በሚያደርጉ ዕሴቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስቴሩ አገራዊ መግባባት እንዲፈጠር በ14 ሺህ ቀበሌዎች ከ20 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፉ የምክክር መድረኮች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!