Fana: At a Speed of Life!

ግለሰቡ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ሽቦ ሲቆርጥ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ግለሰቡ በልደታ ክፍለ ከተማ አብነት የባቡር ፌርማታ ላይ ጨለማን ተገን አድርጎ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ሽቦ ሲቆርጥ እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ከተያዘው ተጠርጣሪ በመነሳትም ተጨማሪ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተረገባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

የወንጀል ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በተለያዩ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ አብነት ፣ዳርማር ፣ልደታ እና ተግባረ-ዕድ የባቡር ፌርማታዎች ላይ ነው።

ኮሚሽኑ እንደገለፀው ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ከአብነት የባቡር ፌርማታ ላይ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ሽቦ ሲቆርጥ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ከተያዘ አንድ ተጠርጣሪ በመነሳትና የምርመራ ቡድን በማቋቋም የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በዚህም በተለያየ ጊዜ በባቡር መስመሩ ላይ ወንጀል ሲፈጽሙ እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲስተጓጎል ሲያደርጉ የነበሩ ተጨማሪ 9 ተጠርጣሪዎች እና ግምቱ ከ 1 ሚሊየን 564 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ተሰርቆ የተቆራረጠ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ሽቦ ተይዞ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከልም አራቱ በዋና ወንጀል ፈጻሚነት፣ ሁለቱ የተሰረቀውን ሽቦ የሚያመላልሱ የላዳ ታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ሶስቱ የተሰረቀውን ሽቦ የሚቀበሉ ሲሆኑ፤ አንደኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ለሌላኛው ተጠርጣሪ ሀሠተኛ መታወቂያ እንዲዘጋጅ ያደረገ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.