የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ታደሰ በአሶሳ ጉብኝት አደረጉ

By Feven Bishaw

May 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት ዓላማ በክልሉ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት አገልግሎት ማሻሻል ላይ ያተኮረ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዋጮ ዋቡልቾ ገልጸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ሚኒስትሯ በሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያ፣ ደም ባንክ ፣ መድሃኒት ኤጀንሲና ሌሎችንም የጤና ተቋማት አገልግሎት ምልከታ አድርገዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!