Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን አዲስ ከተሾሙት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር እና ለአፍሪካ ህብረትና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ ከሆኑት ሃሚድ ኑሩ ጋር ተወያዩ።

አቶ ደመቀ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሃገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሰራሽ ግጭቶች እንዲሁም እንደ ድርቅ በመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ግንባር ቀደም በመሆን እያበረከተ ላለው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም ድርጅቱ የ2020 የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸናፊ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በሆነችበት ወቅት ሌሎች ሁሉንም ነገር ፖለቲካዊ በማድረግ አስተዋጽኦ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብዓዊ እርዳታ በማድረግ የተጫወተው ገንቢ ሚና አንስተዋል።

ለዚህም የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቪድ ቫሲሊ ላሳዩት የመሪነት ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር እና ለአፍሪካ ህብረትና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠሪ ሃሚድ ኑሩ በበኩላቸው ÷ድርጅታቸው ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ወቅት እየተደረገላቸው ለሚገኘው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ አግባብነት ያላቸው ተቋማት ጋር የቅርብ ትብብር እየተደረገላቸው መሆኑንም አንስተዋል።

በአፍሪካ ሃገር በቀል የትምህርት ቤቶች ምገባ ፕሮግራም ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተግባራዊ በተደረጉ ፕሮግራሞች አበረታች ውጤቶችንመመዝገባቸውንም ጠቅሰዋል።

አቶ ደመቀ  መኮንንም በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እስከ ሁለተኛ ዙር ተደራሽ መደረጉንና እና በቅርቡም ሶስተኛ ዙር አቅርቦት ተግባራዊ እንደሚሆን አንስተው÷ ለዚህም የዓለም ፕሮግራም የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ሰላም ማስፈን፣ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ለማካሄድ የተለያዩ ተግባራት እየተካናወኑ መሆኑን አንስተው፥ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት አንጻር ክፍተቶች በመኖራቸው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.