ዘጠነኛው የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሺን ቴክኖሎጅ ኢንስቲቱዩት ባዘጋጀው በዚሁ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ፥ ስለ ጥጥ፣ ጨርቃጨርርቅ፣ አልባሳት ፋሺን እንዲሁም የቆዳ ውጤቶች ጋር የተገናኙ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።
በዚህም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የተለያዩ ተመራማሪዎች የስራ ፈጠራ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቱዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስለሽ ለማ ዘርፉን ለሀገር እድገት መጠቀም እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን ተናገርዋል፡፡
ስራ ፈጣሪዎችን ማሳተፍ የሚያስችል ዘርፍ እንደመሆኑም በጥናት ሊታገዝ እንደሚገባው ጠቅሰው፥ ኮንፈረንሱም ለዚሁ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳነንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራው በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው መሰል ዘርፍ ላይ ለማምጣት የሚያግዙ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት እየተጋ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም መሰል ኮንፈረንሶች ለልምድ ልውውጥ እንደሚያግዙም አንስተዋል፡፡
በዚሁ ኮንፈረንስ የተማሪዎች የተግባር ትምህርት ውጤት በሆኑ ስራዎች የፋሺን ሾው ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!