የባህርዳር ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ በተዘጋጀው የባህርዳር ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ላይ የሚመክር የማህበረሰብ የውይይት መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የተዘጋጀው መዋቅራዊ ፕላን ባህርዳርን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ሊያጎናፅፋት የሚችል መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዬ አለባቸው በከተማዋ የሚታዩ ከህገወጥነት፣ ከአካባቢ ብክለት እና ከመሰረተ ልማት እጥረት ጋር ለተያያዙ ችግሮች መዋቅራዊ ፕላኑ መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ባህርዳር ውብ እና ማራኪ የተፈጥሮ ፀጋን የተላበሰች ከተማ ናት ያሉት ምክትል ከንቲባው መዋቅራዊ ፕላኑ ያላትን ፀጋ በማልማት ለነዋሪዎች ምቹና ዘመናዊ ከተማ እንድትሆን የሚያስችል ነው ብለዋል።
በባህርዳር ከተማ ታሪክ ከዚህ በፊት 3 የከተማ ፕላኖች ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን÷ይህ አሁን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፕላን አራተኛው መሆኑም ተገልጿል።
ፕላኑ ከ40 እስከ 50 ዓመት ሊያግለግል የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት በሚገኘው የውይይት መድረክ መዋቅራዊ ፕላኑ በዝርዝር ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!