ፋና ስብስብ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አንድ ወጣት ባጃጅ ውስጥ ያገኘውን 40 ሺህ ብር እና አልባሳት ለባለቤቱ መለሰ

By Tibebu Kebede

May 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አንድ ወጣት ባጃጅ ውስጥ ያገኘውን 40 ሺህ ብር እና አልባሳት በታማኝነት ለባለቤቱ መለሰ፡፡

በዞኑ ዶዶታ ወረዳ አዋሽ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ዑስማን አደም፥ ባጃጅ ውስጥ ያገኘውን ንብረትነቱ የአቶ አስናቀ አየለ የሆነን 40 ሺህ ብር እና አልባሳት ለባለቤቱ በታማኝነት መልሷል፡፡

ወጣት ዑስማን የንብረቱ ባለቤት ከሆነው አቶ አስናቀ የባንክ ደብተር ባገኘው አድራሻ መሰረት ባለቤቱን በማግኘት፥ ንብረቱን ለበላቤቱ ማስረከቡም ነው የተገለጸው፡፡

አቶ አስናቀ እና ቤተሰቡም ወጣት ዑስማን ላሳየው ታማኝነት ከልባቸው አመስግነዋል፡፡

በሚደቅሳ ቀጫ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!