የሀገር ውስጥ ዜና

በ205 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

By Tibebu Kebede

May 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በዳውሮ ዞን በ205 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ አኖሩ።

የከተማው ነዋሪ የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደነበር ከዚህ ቀደም ለምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር።

ነዋሪዎቹ የህዝቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ መነሻ በማድረግ የክልሉ መንግስት ለሰጠው ፈጣን ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ከህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!