ምርጫ 2013

የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በጀመረባቸው ምርጫ ክልሎች  ምዝገባ ተጠናቋል

By Tibebu Kebede

May 22, 2021

 

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ለ6ተኛው ባወጣው  የጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ ትላንትና ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2013 የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች

በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሲከናወን የነበው ምዝገባ እና የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት በነዚህ ምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ድረስ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሲሆን የመራጮች መዝገባ ቀን ከተጠናቀቀበት ቀን በኋላ ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ አይቻልም መባሉን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!