Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተመስርቷል፡፡

አምባሳደር ፍጹም በአሜሪካ ከሚገኙ ከተለያዩ የእምነት ተቋማት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለተሳታፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል።

በእለቱም የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የዋሽንግተን ዲሲ ቅርንጫፍ በእለቱ ተቋቁሟል።

የጉባኤው መቋቋም የእምነት ተቋማቱ በስራቸው የሚገኙ ምዕመናንን አስተባብረው በአሁኑ ወቅት በአገራችን ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ኢ-ሚዛናዊ ጫና ለመቋቋም እንደሚያግዝም አምባሳደሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፤ የጉባኤው መመስረት በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ወገኖች አንድነት እንዲጎለብት ያደርጋል ብለዋል።

ጉባዔው ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በመሆን የአገርን ጥቅም በማስቀደም ሁሉንም አካታች በሆነ መልኩ እንዲንቀሳቀስም ጠቅላይ ጸሃፊው ገልጸዋል።

በምስረታው የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የእምነት ተቋማት ተወካዮችም በወቅታዊ ጉዳዮች እና ዘላቂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ለጉባኤው ስራ መቃናት የኤምባሰው ድጋፍ እንደማይለያቸውም አምባሳደር ለተሳታፊዎቹ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰባት የእምነት ተቋማትን ያካተተና ከ10 አመት በፊት ተመስርቶ በአገራችን ሰላም፣ አንድነትና መቻቻል እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.