በሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሃመድ የተመራ ልዑክ ጎዴ ከተማ ገባ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሃመድ የተመራው የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጎዴ ከተማ ገብቷል።
ከፕሬዝዳንቱ ጋር የኢፌዲሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለና የኢፌዲሪ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ እንደሚገኙበት ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ልዑኩ ጎዴ ከተማ ሲደርስ በሶማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና በሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፤ የጎዴ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከ475 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የጎዴ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ መጠናቀቁ ይታወቃል።
የውሃው ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ታሪክ የመጀመሪያውና ግዙፍ ሲሆን፤ ግንቦት 14፣ 2011 ዓ.ም ተጀምሮ በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ተጠናቋል።
ፕሮጀክቱ በክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ክትትልና ጉብኝት ሲደረግለት ቆይቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ በጎዴ ከተማ ለዘመናት የነበረውን የንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግርን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፍ ይታመናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!