Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን እያሳየች መምጣቷ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ግምገማ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን እያሳየች መምጣቷ ተገለፀ።
 
የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ ከአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ለደህንነት ኦዲት ከመጡ ዕንግዶች ጋር ተወያይተዋል።
 
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ግምገማ መሠረት 73 ነጥብ 2 እንዳላት የተገለፀ ሲሆን ይህ ነጥብ በዘርፉ ከቀዳሚ ሀገራት ተርታ የሚያሰልፋት ነው ተብሏል።
 
የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ግምገማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱና በየወቅቱ ከሚደረጉ የደህንነት ኦዲት ግመገማዎች ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለዉ መሻሻልና ዕድገት እያሳየች መምጣቷንም ነው የተነገረው።
 
ኢትዮጵያ በድርጅቱ የምታስመዘግበው ውጤት በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ያላትን ተሰሚኒት እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡
 
በተያያዘም የአቪዬሽን ጥንካሬ ለአየር መንገድ ጥንካሬና የመዳረሻ መስፋፋት መሠረት በመሆኑ እስካሁን ያሉትን መደረሻዎች አጠናክሮ ለማቀጠል ይረዳልም ተብሏል፡፡
 
ከዚህ ኦዲት በፊት የአሜሪካ ሲቪል አቭዬሽን በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባደረገዉ ኦዲት ምድብ አንድ ላይ መሆኗን አረጋግጧል፡፡
 
ይህም ተጨማሪ መዳረሻዎችን በአሜሪካና በሌሎችም ሀገራት እንድትከፍት ማስቻሉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.