Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 337 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው እለት 337 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂ ተማሪዎቹ 247 ቱ የደረጃ አራት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሲሆኑ  94ቱ ደግሞ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሞያዎች ናቸው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የደብረ ብርሀን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ÷  ተመራቂ ተማሪዎቹ ሞያው የሚጠይቀው ስነ ምግባር እና ክህሎትን በጠበቀ መልኩ ወደ ስራው አለም ሲቀላቀሉ ለማህበረሰቡ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ በየአመቱ የሚያስመርቃቸው ባለሞያዎች ክልሉ ትኩረት በመስጠት እየሰራበት ያለውን የጤናው ዘርፍ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት እና ማህበረሰቡ የጣለባቸውን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኤልያስ ሹምዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.