የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም “ሲንቄ ባንክ” ተብሎ ተመሰረተ

By Meseret Awoke

May 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ በማደግ “ሲንቄ ባንክ በመባል ዛሬ ተመስርቷል፡፡

በምስረታው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ አባገዳዎች፣ ሐደ ሲንቄዎችና የባንኩ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ባንኩ በ7 ቢሊየን ብር ካፒታል የተመሰረተ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ዘውዴ ተፈራ ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ከ15 ቢሊዮን በላይ ጠቅላላ ሀብት እንዳለው የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ ተወዳዳሪ ባንክ ለመሆን እንደተዘጋጀም አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ በከፍተኛ ካፒታል መመስረቱ የተለየ ያደርገዋልም ብለዋል፡፡

ባንኩ የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም የነበሩትን 400 ቅርንጫፎች እንደሚጠቀምባቸው ተገልጿል።

ተቋሙ ላለፉት 24 ዓመታት የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ኢዜአ ዘገቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!